በውይይታቸው ወቅት ክቡር አምባሳደር ስለወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ ያስረዱ ሲሆን፣ Dr. Gabriele Goldfuß በበኩላቸው በአዲስ አበባ እና ላይፕዚሽ ከተሞች መካከል ባለው የእህትማማች ከተሞች ግንኙነት ማዕቀፍ የተከናወኑ ፕሮጀክቶችን በመዳሰስ ቀጣይ ስለሚሰሩ ተግባራት አስረድተዋል።
ክቡር አምባሳደርም በሁለቱ ከተሞች ጉድኝት ማዕቀፍ ስለተከናወኑ ፕሮጀክቶች ያላቸውን አድናቆት ገልጸው በቀጣይም ግንኙነቱን በተለያዩ ዘርፎች ለማስፋት በተለይም ከንግድና ቱሪዝም ጋር በተያያዘ በጋራ ለመስራት መክረዋል።
አዲስ አበባ እና ላይፕዚሽ ከተሞች መካከል የእህትማማች ከተሞች ጉድኝት የተመሰረተው እ.ኤ.አ. በ2004 ነው።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook