ክቡር አምባሳደር በውይይታቸው ወቅት የሃገራችንንና የቀጠናውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ተወካዩ የክልሉ ባለሃብቶች በአገራችን በተለያዩ የኢንቨስትመንትና የንግድ መስኮች እንዲሳተፉ፣ የተለያዩ ከተሞች የንግድ ምክር ቤቶች ከአገራችን አቻ ምክር ቤቶች ጋር በትብብር መስራት እንዲችሉ፣ የክልሉ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማትም ከሃገራችን አቻዎቻቸው ጋር መደጋገፍ የሚችሉበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹ እንዲሁም እህትማማች ከተሞችንም መፍጠር እንዲቻል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ሚኒስትር ዴኤታ Dr. Mark Speich በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት የማዕዘን ድንጋይ እንደሆነች እንደሚገነዙና የክልሉ የተለያዩ ተቋማት ከሃገራችን የትምህርት፣ የምርምር፣ የንግድ ተቋማት ጋር በጋራና በትብብር መስራት እንዲችሉ ፍላጎት እንዳላቸውና ይህንንም ለማሳካት ከኤምባሲው ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
የሰሜን ራይን ቬስትፋሊያ(North Rhine-Westphalia) በጀርመን ካሉት 16 ክልላዊ መንግስታት ውስጥ በኢኮኖሚ ቀዳሚው ነው።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook