Diaspora Overviews

    ቀረጥ ነፃ

     እባክዎ ከቀረጥ ነፃ ደብዳቤ አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ/እንድንልክልዎት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ        ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ይቅረቡ/ይላኩ፡፡ 

  1. አገልግሎቱን ለመጠየቅ አንድ አመትና ከዚያ በላይ በውጭ አገር የኖሩ መሆን ይኖርብዎታል፡፡ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ፤ 
  2. የነበሩበትን ስራ መልቀቅዎትን የሚያመለክት ደብዳቤ ወይም ድርጅት ከሆነ የተዘጋ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ፤ 
  3. ኢትዮጵያዊ ለሆኑ  ፓስፖርት ኮፒ እና የመኖሪያ ፈቃድ መመለስዎትን የሚያሳይ ማስረጃ ኮፒ፤ 
  4. ኢትዮጵያዊ ካልሆኑና የጀርመን አገር ዜግነት ካለዎት የጀርመን ፓስፖርት እና የትውልደ መታወቂያ ኮፒ እንዲሁም የመኖሪያ ፈቃድ መመለስዎትን የሚያሳይ ማስረጃ ኮፒ  
  5. የሚያስገቡትን እቃዎች ዝርዝር  
  6. የማመልከቻ ቅጽ  
  7. የቃለ መሀላ ቅጽ   
  8. ተማሪ ከሆኑ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ፤  ትምህርት ማጠናቀቅዎትንና መታወቂያ መመለስዎትን የሚገልጽ ማስረጃ ከትምህርት ቤቱ በደብዳቤ ማቅረብ እንዲሁም የመኖሪያ ፈቃድ መመለስዎትን የሚያሳይ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ፤ 
  9. ባለጉዳዮች ከላይ የተጠየቀሰውን አገልግሎት በፖስታ ማግኘት ከፈለጉ ከላይ የተጠየሱትን ማስረጃዎች በማሟላት ለኤምባሲው በአድራሻ ከመመለሻ ፖስታ ጋር ማለትም ቴምብር እና አድራሻ የተገለፀበት ፖስታ አብሮ በመላክ አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉ ይሆናል፡፡ 

        በማህበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት የሚያስፈለጉ መስፈርቶች  

  1. በማህበር የተደራጁበትን የሚያሳይ ህጋዊ እና በኤምባሲው የተረጋገጠ ሰነድ ማቅረብ፤ 
  2. የማህበሩን ስም፤ የማህበሩ አድራሻ እና የአባላት ዝርዝር ከአባላት ፓስፖርት እና መታወቂያ ኮፒ ጋር መቅረብ አለበት ፤ የማህበሩ ሰብሳቢ እና ፀሐፊ ስልክና ኢሜይል መጠቀስ አለበት፤ 
  3. ከእያንዳንዱ የማህበር አባል ፓስፖርት ኮፒ እና መታወቂያ ኮፒ መቅረብ አለበት፤ 
  4. የድጋፍ ደብዳቤ ከኤምበሳሲው ለማግኘት በማህበር ተደራጀተው ቤት መስራት እንደሚፈልጉ ማመልከቻ  ማቅረብ  
  5. አዲስ አበባ ተወካይ ያስፈልጋቸዋል፤ ዳያስፖራ አገልግሎት ሄዶ ተከታትሎ ለሚመለከተው አካል ለምሳሌ ለአዲስ አበባ ወይም ለክልሎች  የሚሰጠውን ደብዳቤ ተቀብሎ የሚያስተላለፍ 
  6. ከላይ የተጠቀሱት ከተሟሉ በኤምበሳሲው በኩል  የድጋፍ ደብዳቤ ይፃፋል 

ኢንቨስትመንት

የሚያስፈለጉ መስፈርቶች
1 የኢትዮጰያ ፓስፖርት እና የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ
2 በትውልደ ኢትዮጰያዊ ለሆኑ ደግሞ የትውልደ ኢትዮጵያ መታወቂያ ኮፒ እና የመኖሪያ ፈቃድ
 
 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook