በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚከሰት ወሳኝ ኩነት መመዝገብ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሠረት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ በኢሚግሬሽን፣ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በውጭ የኢትየጵያ ኤምባሲዎች በቆንስላዎች አገልግሎት በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚከሰት ወሳኝ ኩነት መመዝገብ እንዲችል ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ በዚህም መሠረት በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚከሰት ወሳኝ ኩነት ለመመዝገብ የምዝገባ አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 7/2010 ሥራ ላይ ውሏል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ በበርሊንና አካባቢ እንዲሁም ኤምባሲው የሚሸፍናቸው ቼክ ሪፑብሊክ፣ ፖላንድ፣ ስሎቫክያና ዩክሬን የምትኖሩ ኢትጵያውያን የጋብቻ እና የልደት ካርድ ኩነቶችን በኤምባሲያችን አማካይነት ማስመዝገብ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡ ከታች የተገለፀውን መስፈርቶች አንብባችሁ ማሟላታችሁን ካረጋገጣችሁ abachew.mekonnen@aethiopien-botschaft.de ላይ ስማችሁን በመግለጽ ቀጠሮ ማስያዝ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡
የጋብቻ ምዝገባ
ቅድመ–ሁኔታዎች
- ተጋቢዎች ጋብቻ ለመፈጻም ማስባቸውን እጅግ ቢዘገይ ጋብቻቸውን ለመፈጸም ከወሰኑበት ቀን ከአንድ ወር በፊት ለቆንስላ አገልግሎት ክብር መዝገብ ሹም ማስታወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ይህ ድንጋጌ በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥርዓት የሚፈጻም ጋብቻን አይመለከትም፡፡
- የቆንስላው የክብር መዝገብ ሹሙ ጥያቄው በቀረበለት ቀን ከተጋቢዎቹ ጋር በመነጋገር ከወሰነ በኃላ በማግሥቱ ጋብቻው የሚፈጻምበትን ቀን በመግለጽ አመቺ በሆነው መንገድ ለ15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ማስታወቂያ ያወጣል ወይም በሚሲዮኑ ዌብ ፔጅ እና በሶሻል ሚዲያ ላይ ያሳውቃል፡፡
- ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጋብቻ መቃወሚያ በጽሑፍ መቅረብ አለበት፤ መቃወሚያ ሊያቀርብ የሚችሉ ወላጆችና ተወላጆች፣ አቃቤ ሕግ፣ አሳዳሪ ወይም የቀደመ ጋብቻ አለኝ የሚልሰው መሆን አለበት።
- የክብር መዝገብ ሹሙ በቀረበው የጋብቻ መቃወሚያ ላይ በአምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውሳኔ በመስጠት ማሳወቅ አለበት፡፡
- ወንድም ሆነ ሴቷ 18 ዓመት ሳይሞላቸው ጋብቻ መፈጸም አይችለም።
- ጋብቻ ህግ በሚከለክላቸው የሥጋና የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል መፈጸም የተከለከለ ነው፡፡
- ተጋቢዎች በፍርድ ቤት እንዳያገቡ የተከለከሉ መሆናቸውን የሚገልጽ የጽሑፍ ማስረጃ የተገኘ እንደሆነ የክብር መዝገብ ሹሙ ጋብቻውን አይመዘገብም፡፡
- ማንኛውም ጋብቻ በፌዴራል ወይንም የቤተሰብ ሕግ መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- በባህል መሠረት የሚፈጻም ጋብቻ አንድ ወንድና አንዲት ሴት በሚኖሩበት አካባቢ ባህል ወይም በሁለቱ ተጋቢዎች ወይንም ከሁለቱ ተጋቢዎች በአንዳቸው ባህል መሠረት የተፈጻመ መሆን አለበት፡፡
- አንዲት ሴት በብቸኝነት ለመኖር በህግ የተወሰነው ጊዜ ሳያልፍ ከሌላ ወንድ ጋር ጋብቻ መፈጸም አትችልም፡፡
- የሚፀና ጋብቻ ተፈፀመ የሚባለው ተጋቢዎቹ ለመጋባት ነፃና ሙሉ ፈቃዳቸውን ሲሰጡ ብቻ ነው፡፡
- በሙሽራው በኩል 2 በሙሽሪት በኩል 2 በድምሩ 4 ምስክሮች መቅረብ አለባቸው፡፡
ደጋፊ ማስረጃዎች
- ጋብቻው የሚፈፀመው በሚኖሩበት አካባቢ ከሆነ የነዋሪነት ማስረጃ የተሰጠ መታወቂያ ማቅረብ አለበት፡፡
- የተጋቢ ምስክሮች አገልግሎቱ ያላለፈበት የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
- ሙሽራዋ/ው ከዚህ በፊት አግብታ/ቶ የፈታ/ች ከሆነ የፍቺ ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት፡፡
- ሙሽራዋ/ው ከዚህ በፊት አግብታ/ቶ የሞተችበት/ባት ከሆነ የሞት ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት፡፡
- ከ6 ወር ወዲህ በተመሳሳይ ጊዜ የተነሱት ሁለት 3 በ 4 ሳ.ሜ የሆነ የተጋቢዎች ፎቶግራፍ መቅረብ አለበት፡፡
- በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥርዓት የተፈፀመ ጋብቻ የተጋቢዎች ምስክሮች ወይም በጋብቻ ሥርዓቱ ላይ የታደመ ሰው በክብር መዝገብ ሹሙ ፊት በአካል ቀርበው ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው፡፡
የተጋቢዎች የልደት ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት፡፡
የልደት ሰርተፊኬት
- የከተወለዱበት ሆስፒታል ማስረጃ
- የእናት ወይንም የአባት ፓስፖርት እና የሚኖሩበት ሀገር መታወቂያ
- 1 ፎቶ ግራፍ
- ክፍያ ዩሮ 49