የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የንግድ ተስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በበርሊን 25th Years Anniversary German Managers Meeting የተዘጋጀ ስብሰባ ላይ የነበራቸውን ተሳትፎ ካጠናቀቁ በኋላ በርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተገኝተው ከዲፕሎማቶች ጋር ተወያይተዋል ::
በነበረው ውይይትም ኢትዮጵያ አገራችንን ወደ ፊት ለማራመድ የሚችሉ እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚ ሀገራዊ ስራዎችን በተመለከተ በክቡር ሚኒስትሩ አጠቃላይ ገለጻ ተደርጓል::
የክቡር ሚኒስትር ደኤታ ገለጻ ተከትሎም ሚሲዮኑ የተሰጠውን አገራዊ ተልዕኮ ለመወጣት በሚያደርገው የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ፣ በንግድ ትስስር ውስጥ ያሉ ጉዳዮች በተመለከተ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያም ሚኒስትር ደኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በኩል ማብራራያና የማጠቃለያ ምላሽ ተሰጥቷል::

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook