GERD (grand ethiopian renaissance dam)

1. የታላቁ የኢትየጵያ ሕዳሴ ግድብ ቦንድ ለመግዛት የሚያስፈልግ መረጃ

·        ቦንድ ገዢዉ በቅድሚያ ወደ ኤምባሲ /ቤት በመሄድ የቦንድ ግዥ ቅጽ ይሞላል፣

·        መታወቂያ ኮፒ ተደርጎ ይያዛል

·        ገዢዉ ክፍያዉን በኤምባሲ በካሽ ይፈጽማል

·        ክፍያዉን ሲፈጽም ወዲያዉ ቦንዱን ከኤምባሲዉ ያገኛል ቦንድ በባንክ ገንዘቡን በማስተላለፍ መግዛት ይቻላል

Embassy of Ethiopia

DE34100400000267396000 (የቦንድ ብቻ አካዉንት ነዉ)

2. የሚፈለጉት የቦንድ ዋጋ ከላይ በላዉ አካዉንት በማስገባት

የመታወቂያ ኮፒ እና የከፈሉበትን ደረሰኝ ከመመለሻ ፖስታ ጋር በማድረግ ወደ ኤምባሲ መላክ ይቻላል።

ቦንዱ ከደረሰኝ ጋር በአድራሻዎ ይላክሎታል።

3. የቦንድ ወለድ አጠቃቀም እና አከፋፈል

  • የወለድ ክፍያ የሚፈጸመዉ የቦንዱ ግዥ የተፈጸመበትን የምንዛሪ ዓይነቶች መነሻ በማድረግ በዩሮ ይሆናል
  • ገዢዉ የክፍያ ጊዜ ሲደርስ በግንባር በመቅረብ ወይም በሕጋዊ ወኪል መውሰድ ይችላል
  • ኤምባሲዉ ወደ ኢትየጵያ ንግድ ባንክ ደብዳቤ ይጽፋል
  • ለሌላ ተጨማሪ ቦንድ ግዢ ማዋል ይችላል
  • በዉጭ ምንዛሪ ወይም በብር በሚከፍተዉ ሒሣብ ገቢ ሊያደርግ ይችላል
  • ለተለያዩ ክፍያዎች ሊጠቀምበት ይችላል።

4. የቦንድ ዋጋ

  • የ 50 ፣ 100 ፣ 300 ፣ 500 ፣ 1000 ፣3000 ፣ 5000 ፣ 10,000 ዋጋ ያላቸዉ ቦንዶች ለሽያጭ ቀርቧል።

5.  የቦንድ ወለድ

ሀ. ባለ 5 ዓመት – LIBOR + 1.25%

ለ. ባለ 6 ዓመት – 7 ዓመት – LIBOR + 1.5%

ሐ. ከ8 – 10 ዓመት – LIBOR + 2%

ማሳሰቢያ ፡- ከወለድ ነጻ መግዛት ይቻላል።

– ከ50 ዩሮ በታች በስጦታ መለገስ የሚፈልጉ ደረሰኝ ብቻ በመዉሰድ ለግድቡ ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ቦንድ ለመግዛት የቃል መግቢያ ቅጽ

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook