በጀርመን እና ሚሲዮኑ በሚሸፍናቸዉ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን የተሳተፉበት ታላቁ የህዳሴ ግድብ የተጀመረበት 13ኛዉ ዓመት መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም በበይነ መረብ በፓናል ዉይይት በበርሊን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ በድምቀት ተከብሮ ውሏል:: የፓናል ዉይይቱን በንግግር የከፈቱት በጀርመን እና ሚሲዮኑ በሚሸፍናቸዉ አገራት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕከተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ባስተላለፉት መልዕክት መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የተጀመረዉ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ተሳክቶ ከመገባደጃዉ ጫፍ ደርሰዋል ካሉ በኃላ ግደቡ እጅግ በጣም ብዙ ችግሮችን፣ፈተናዎችን እና የሴራ ወጥመዶችን አልፎ ከዚህ ስኬት መድረሱ߹ግድቡ በራሳችን ወጪ መስራታችን የኢትዮጵያዉያን የጀግንነት እና የአይበገሬነት ማሳያ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ኩራትና የይቻላል ተምሳሌት ነዉ ብለዋል ፡፡ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ከዚህ ቀደም ሲያደርጉት እንደነበረዉ የግድቡ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸዉን አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመቀጠል የዕለቱ የክብር እንግዳ በአሜሪካ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕከተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪ የሆኑት ደ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በፓናል ውይይቱ ለተሳተፉ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን እና ለሚሲዮናችን ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል። ክቡር አምባሳደር ስለሺ በቀለ በገለጻቸዉ ” ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት የኢነርጂ ጠቀሜታ” ፣ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የአገራችንን የኢነርጂ ይዞታ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግ አና የኢትዮጵያ የሃይድሮ ሀብት አለኝታ መሆኑን፣ የህደሴ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ ለቱሪዝም ያለዉ ጠቀሜታ፣ኢትዮጵያ ያልተሳተፈችበትና በማትቀበለዉ የ1959 ስምምነታቸዉ የናይል ዉሃን ግብፅና ሱዳን ኢትዮጵያን በማግለል በብቸኝነት ተከፋፍለዉ ሲጠቀሙበት መቆየታቸዉን እና የግድቡ ግንባታ በመጀመራችን ያለፍንባቸዉ ፈታኝ ሁኔታዎች በሕዝባችን አንድነትና ፅናት እንዲሁም በለዉጡ በመንግስታችን ጥብቅ ክትትል እና ቆራጥ አመራር የግድቡ ግንባታ ወደ መገባደድ መድረሱን ገልጸው ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ዳያስፖራዎች ቀሪዉን የግድቡ ግንባታ ከፍጻሜ ለማድረስ ከዚህ በፊት ሲያደርጉት እንደነበረዉ ድጋፋቸዉን አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም በፓናል ዉይይቱ የተሳተፉት ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ የኢትዮጵያዉያን በርካታ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን በዕለቱ ፓናሊስት ለጥያቄዎቹ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል:: ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ የኢትዮጵያዉያኑም የግድቡ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በገንዘባቸውና በእውቀታቸው የሚጠበቅባቸውን ድጋፍና አስተዋጽዎ እንደሚያደርጉ ቃል በመግባት የፓናል ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook