በፍራንክፈርት ለሁለት ቀናት በተካሄደ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎቻችን እንዲሁም ለሀገር ልማት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ የቆዩ ሴቶች ስራዎቻቸውን የማስተዋወቅና የልምድ ልውውጥ ያደረጉ ሲሆን በመቀጠልም ኖቬምበር 17 ቀን 2024 የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር(EDWA) ምስረታ ጉባኤ በማካሄድ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ማህበሩን የሚመሩ ሰባት አባላት ያሉት የማህበሩ አመራሮችን በመምረጥ ተጠናቋል። በማህበሩ ምስረታ ሂደት ላይ ኤምባሲው ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፣ በምስረታ ጉባዔው ላይ በመገኘት ማህበሩ ለሀገር ልማት በሚያደርገው አዎንታዊ አስተዋጽኦ የኤምባሲው ድጋፍ እንደማይለያቸው አርጋግጧል።