ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በጀርመን ፌደራል መንግስት የBaden-Württemberg ሴክሬተሪ ኦፍ እስቴት ከሆኑት Mr. Rudi Hoogvliet ጋር በኢትዮጵያና በክልሉ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ክቡር አምባሳደር በኢትዮጵያና ጀርመን መካከል ስላለው ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማብራሪያ ሰጥተው ተወካዩ በበኩላቸው የBaden-Württemberg ክልል በኢትዮጵያ ጽ/ቤት እነዳለው ገልጸዋል። በውይይቱ ወቅት ክልሉ ከአገራችን ጋር በኢንቨስትመንት፣ ንግድ፣ ቱሪዝም እና ሌሎች ሴክተሮች ትብብር ለማጠናከር እንዲቻል በክልሉ የዓለምአቀፍ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ከሚሰራው BW International የተሰኘ መንግስታዊ ኤጀንሲ ጋር በቅንጅት በመስራት በታዳሽ ኃይል ልማት በhydropower፣ hydrogen energy፣ solar energy፣ እንዲሁም geothermal energy ረገድ አገራችን ላይ እንዲሳተፉ በጋራ እንደሚሰሩ ፣Goethe Institut ተጨማሪ ማዕከል በሚከፍትበትና የጀርመን Skilled Immigartion Act ለዜጎቻችን በሚኖረው እድል ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook