ክቡር አምባሳደር በውይይታቸው ወቅት የሃገራችንንና የቀጠናውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ገለፃ በማድረግ ፋውንዴሽኑ ከአገራችን መሰል ተቋማት ጋር በትብብር መስራት እንዲችልና በሲቪክና ፖለቲካ፣በተለያዩ የቢዝነስ አማራጮች ለአገራችን ባለሙያዎች ስልጠና እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡
Dr. Rene Klaff በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እያደረገች ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ እንደሚያደንቁና ፋውንዴሽኑ ወደፊት ፋውንዴሽኑ በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ መድረኮች ከኤምባሲው ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።