(ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም) በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የሀገራዊ ፕሮጄክቶች ሚኒስትር ደኤታ አቶ ከድር አብዱራህማን ለሥራ ጉዳይ ወደ ጀርመን በመጡበት ወቅት በርሊን ከሚገኙ የሚሲዮኑ ዲፕሎማቶች ጋር ተወያይተዋል ።
በነበረው ውይይትም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ኢንሼቲቭ እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና ሀገራዊ ፕሮጄክቶችን በተመለከተ በክቡር ሚኒስትሩ አጠቃላይ ገለጻ ተደርጓል::
በዉይይቱ ወቅትም የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች አካል የሆኑት እንጦጦ ፣ አንድነት ፓርክ፣ የወዳጅነት ፓርክ ፣ ጎርጎራ ፣ ወንጪ፣ ሐላላ ኬላ ፣ ኮይሻ ሲሆኑ ገበታ ለትውልድ ደግሞ ከክብር ጠቅላይ ሚኒስትር የመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የሚደገፍ ሆኖ በሁሉም ክልሎች የሚተገበር መሆኑን ገለጻ አድርገዋል ሚኒስትሩ ።
የክቡር ሚኒስትር ገለጻ ተከትሎም ሚሲዮኑ እነዚህን የአገራችንን ገጽታ ሊቀይሩ የሚችሉ ፕሮጄክቶችን የግንዛቤ ማስጨበጥ እና ማስተባበር የድርሻውን ለመወጣት የሚያግዙ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያም ሚኒስትር ደኤታ አቶ ከድር አብዱራህማን በኩል ማብራራያና የማጠቃለያ ምላሽ ተሰጥቷል::