ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ከProfessor Schlauderer እንዲሁም ከዶ/ር ስታየሁ ይገረም የዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ Director, School of Animal and Range Sciences ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት አድርገዋል፡፡
Professor Schlauderer በውይይታቸውም በየአየር ንብረት ለውጥና በምግብ ዋስትና ረገድ በሁለቱ ዩኒቨርስቲዎች እየተሰሩ ስላሉት ፕሮጀክቶች አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም በማስተር ፕሮግራም፣ በሪሰርች እንዲሁም የተለያዩ ሥልጣናዎች ለኢትዮጵያውያን እየተሰጠ መሆኑንና የህም የግብርና ምርታመነትን በማሳደግና ከዚሁ ጋር ተያያዥ የሆኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማከናወን እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ስንታየሁም በበኩላቸው በግብርና ዘርፍ የሚሰጠው ትምህርት ወደ ተግባር በመቀየር በአገራችን በግብርናው ዘርፍ የተሻለ እድገት እንዲመጣና ከኢንዱስትሪው ጋር ለማገናኘት እንደሚያግዝ፣ ለዚህም ከጀርመን ልምድ መቅስም አንደሚቻል አንስተዋል፡፡
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2023 የመጀመሪያውን አምስት ዓመት ፕሮግራም በመገምገም ቀጣዩን የአምስት ዓመት መርሃ ግብር ሥላ ላይ ለማዋል በዝግጅት ላይ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ክቡር አምበሳደር ፍቃዱ ከጀርመን መንግስት ጋር ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን ገልጸው፣ ግብርናም በኢትዮጵያ ቅድሚያ የሚሰጠው ሴክትር እንደመሆኑ መጠን ከጀርመን ጋር በጋራ የምንሰራበት እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ በቀጣይም በዩኒቨርስቲዎቹ ለታሰቡ ዎርክሾፖችና የተለያዩ ፕሮጀክቶች ኤምባሲው አስፈላጊውን ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠውላቸዋል፡፡
ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በተጨማሪ በባህርዳርና በአርሲ ጀርመን የሚገኘው ዩኒቨርስቲ በጋራ እየሰራ መሆኑንና ቁጥራቸው ከሃምሳ በላይ የሚሆኑ ከኢትዮጵያ የስኮላርሽፕ ተጠቃሚ መሆናቸውን ከተደረገው ውይይት ለማወቅ ተችሏል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook