ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በፋውንዴሽኑ እየተደረገ ያለውን ድጋፍ በማመስገን በመቀጥልም የወቅታዊ የአገራችንን ሁኔታ አስረድተዋል። አያይዘውም ከፋውንዴሽኑ ጋር ፓርላማ ከፓርላማ ጉድኝት፣ በምርምርና በስልጠና በጋራ ለመስራት መክረዋል፡፡ከጀርመን ባለሀብቶችም ጋር እንደሚያገናኙን ገልፀዋል ።
H.E. Schulz በበኩላቸው አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤታቸው በኩል በስልጠና በመሳሰሉት ረገድ እየሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም ፓርላማ ከፓርላማ ልውውጥና በሌሎችም መስክ አብሮ ለመስራት እንደሚሹ ገልጸዋል።
H.E. Schulz የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንትና የጀርመን ፓርላማ አባል በመሆን ረጅም ግዜ ያገለገሉ ሲሆን፣ ልዑካን ይዘዉም ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል፡፡በቀጣይም ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተናግረዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook