ይህ የተገለጸው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የሚመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ሁለቱ ከተሞችን በጎበኙበት እና የልምድ ልዉዉጥ ባደረጉበት ወቅት ነው ።
የStuttgart ከተማ ከንቲባ Dr.Alezandra Submann እና የSchwabisch Gmund ከንቲባ Mr.Richard Arnold የኢትዮጵያን ከተሞች በትምህርትና ሥልጠና፣ ከተማን በማዘመን፣ በከተማ ልማት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል ፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ከሁለቱ ከተሞች ከንቲባ ጋር የተወያዩ ሲሆን ከልዑካን ቡድኑ ጋር ተዘዋውረው የከተሞቹን መሠረተ ልማቶች ጎብኝተዋል።
ክብርት ሚኒስትሯ ከልዑካን ቡድናቸዉ ጋር ጀርመን ሲደርሱም በጀርመን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍቃዱ በየነ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ሚኒስትሯ በቆይታቸው በከተሞች የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ የተወያዩ ሲሆን የSchwabisch Gmund የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መዝገብ ላይ የክብር ፊርማቸውን አኑረዋል ፡፡
በሌላ በኩል በበርሊን በነበረዉ የልዑካን ቡድኑ ቆይታ ክብርት ሰመሪታ ሰዋሰው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ከጀርመን ፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር Director General European International Financial policy Dr. Judith Hermes እና ከጀርመን የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር GIZ ,KFW ተወካዮች ጋር በሁለትዮሽና በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይታቸውም ክብርት ሰመሪታ ሰዋሰው ወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታንና በአገራችን በተለያዩ ሴክተሮች የሪፍርም ሥራዎች እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራትን ገለፃ አድርገውላቸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ሌላው የልዑካን ቡድኑ አካል በበርሊን በነበረው ቆይታ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ ከጀርመን ንግድና ኢንዱስትሪ ቻምበር (DIHK) የአፍሪካ ዳይሬክተር ከሆኑት Mr. Heiko Schwiderowski ጋር የሁለትዮሽ ንግድ ማስፋፋት በሚቻልበት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በተጨማሪም የፋይናንስ ዘርፉን በተመለከተ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን የጋራ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት ሀሳብ ተለዋውጠዋል::