The Open Day 2023 ቀንን ምክንያት በማድረግ በበርሊን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲና የጀርመን የኢኮኖሚ :የልማትና ትብብር ሚኒስቴር (BMZ) ትብብር የቡና ምርት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የትሪዝም መዳረሻዎች የማስተዋወቅ ፕሮግራም በበርሊን የጀርመን የኢኮኖሚ :የልማትና ትብብር ሚኒስቴር (BMZ) ዋና መ/ቤት ግቢ ውስጥ ተዘጋጅቷል፡፡
በበርሊን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ባዘጋጀው የቡና ጠጡ ሴሪሞኒ ተቀማጭነታቸውን በርሊን ያደረጉ የዓለም አቀፍ ተቋማት እና የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች የኢምባሲ አባላት እንዲሁም የBMZ ሠራተኞች ዝግጅቱን ታድመዋል፡፡
በጀርመን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ዝግጅቱን ተገኝተው የከፈቱ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ የቱሪስት መዳረሻዎች ባለቤት መሆኗን በመጥቀስ በኢትዮጱያ ብዙ ተወዳጅ የሆነዉን ቡና ከትውልድ ቦታው ተገኝተው እንዲቀምሱ እና ኢትዮጵያንም እንዲጎበኙ ታዳሚውን ጋብዘዋል ፡፡ የጀርመን የኢኮኖሚ :የልማትና ትብብር ሚኒስቴር (BMZ) ጊቢ ውስጥ በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ቡና ሴሪሞን ከ2ሺህ በላይ ታደሚዎች በቦታው ተገኝተው የኢትዮጵያን ቡና የቀመሱ ሲሆን ስለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የትሪዝም መዳረሻዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል ።
በተጨማሪም ክቡር አምባሳደሩ የጀርመን የኢኮኖሚ :የልማትና ትብብር ሚኒስቴር (BMZ) ሚኒስትር H.E Mrs. Svenja Schulze የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች ጋር ያደረጉት ውይይት ላይ የተገኙ ሲሆን ለክብርት ሚኒስትሯ ጀርመን ዋነኛ የልማትና የትብብር አጋራችን መሆኗን በመግለጽ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook