(ኀዳር 21,ቀን 2017 ዓ.ም:በርሊን ): በጀርመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ኤምባሲ ዲፕሎማቶች እና ሠራተኞች እንዲሁም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ አባላት 19ኛውን የብሔር ፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል አክብረዋል።
በዕለቱ ክቡር አምባሳደር እስክንድር ይርጋ በጀርመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ኤምባሲ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልእክተኛ ባስተላለፉት መልእክት ኢትዮጵያ የብዝሐ ማንነት መሰባሰቢያ መሆኗን ገልጸው ዳያስፖራው ለአገራችን ብሔራዊ መግባባት እና ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት አውንታዊ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥራ አስተላልፈዋል ።
ክቡር አምባሳደሩ አያይዘውም ኤምባሲው ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ጋር የበለጠ ተቀራርቦ በመስራት በዲፕሎማሲው መስክ እንደ አገር የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አጠናክሮ ለመቀጠል በአንድነት እና በትብብር መንቀሳቀስ እንደሚገባ አስገንዝበው ኤምባሲውም አብሮነትን ለማጎልበት ዝግጁነቱን ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል ።
በበዓሉ ላይ ለ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን የተዘጋጀ “ኅብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት በኢትዮጵያ፣ ተግዳሮቶቹ እና የመፍትሄ ሀሳቦቹ !” የሚል ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።