በጀርመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ከጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር Managing Director Ms.Claudia Voß ጋር ጁን 06, 2023 ተወያይተዋል ።
በዉይይቱ ወቅትም ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ የጀርመን አፍሪካ ቢዝነስ ማህበር በኢኮኖሚ ዘርፍ የጀርመንን እና የአገራችንን የሁለትዮሽ ትብብር ለማሳደግ የሚሰሩትን ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ አመስግነው በተለይ የጀርመን ኢንቨስተሮች ወደ አገራችን በመሄድ አገራችን ያላትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና እድሎችን በመጠቀም ኢንቨስት እንዲያደርጉ እያደረጉ ያለውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ የበለጠ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። በተጨማሪም በቀጣይ ወራት በጀርመን የኢትዮ-ጀርመን የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ለማዘጋጀት በሚደረገው ስራ ላይ በተባባሪነት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበውላቸዋል።
ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ Ms.Claudia በበኩላቸው በአገራችን እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት አንስተው በFederal Chancellor of the Federal Republic of Germany በተጠራው G20 Compact with African Conference አገራችን መጋበዟን ገልጸው በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ በበለጠ በጋራ ለመስራትና የታቀደውንም የኢትዮ-ጀርመን ፎረም ለማሳካት በሁሉም አግባብ ተባብሮ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል ።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook