በጀርመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ከጀርመን የንግድ ማህበራት ምከርቤት (DIHK) የስራ ሃላፊ ከሆኑት Mr. Heiko Schwiderowski Director of Africa at DIHK፤እና ከ Ms Lisa Reymann Director of Sub- Sahara Africa ጋር ጁን 8 ቀን 2023 ተወያይተዋል።
ክቡር አምባሳደሩ ከሥራ ሓላፊዎቹ ጋር ሀገራችን በጀርመን ለማካሄድ ላቀደችው ኢትዮ -ጀርመን የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ፣ በመጪው ወራት በጀርመን በርሊን በFederal Chancellor of the Federal Republic of Germany በተጠራው G20 Compact with African Conference እና ኢትዮጵያ ላይ የጀርመን የንግድ ማህበራት ምክር ቤት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዙሪያ በሚሉ ጉዳዮዮች ላይ ዉይይት አድርገዋል ።
የሥራ ሓላፊዉ Mr. Heiko Schwiderowski Director of Africa Ai DIHK በ G20 Compact with African Conference ከሀገራችን ለሚሳተፉ የሀገር መሪዎች እና የስራ ሃላፊዎች የጎንዮሽ የቢዝነስ ውይይት እንደሚያመቻቹ ለክቡር አምባሳደሩ ገልጸውላቸዋል።
ክቡር አምባሳደሩም ኢትዮጵያ በጀርመን የቢዘነስ ፎረም ለማካሄድ ላቀደችዉ የምክር ቤቱን ድጋፍ የጠየቁ ሲሆን በመጨረሻም የጀርመን የንግድ ማህበራት ምክር ቤት የአፍሪካ ዋና ዳይሬክተሩ ጀርመን በኢትዮጵያ የንግድ ም/ቤት ለመክፈት የጀመረችዉን ዳር እንዲደርስ የበኩላቸዉን አስተዋፅኦ እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል።