ክቡር አምባሳደር ፈቃዱ የጀርመን ትራቭል አሶሴይሽን የኢትዮጵያን ቱሪስት መዳረሻዎችን ለጀርመን የቱሪዝም ገበያ በሰፊው ለማስተዋወቅ ለሚያደርጉት አስተዋጽኦ አመስግነዉ በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ከአምስቱ የትኩረት መስኮች አንዱ መሆኑንና እንደሀገር ዘርፉን ለማሳደግ እየተሰራ እንደሆነ ለሓላፊዉ ገልጸውላቸዋል ።

በውይይቱ ወቅትም Mr. Volker Adams የሀገራችንን የቱሪዝም አማራጮች ለጀርመን ገበያ ለማስተዋወቅ 14 የጀርመን የጉዞ ወኪሎችና አስጎብኚ ድርጅቶችን የያዘ የልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክና የቱሪዝም ገበያ ጥናት ፎረም ኢትዮጵያ ላይ ለማካሄድ ስምምነታቸዉን ለክቡር አምባሳደሩ ገልጸዉላቸዋል ።

አክለዉም የጀርመን ትራቭል አሶሴሽን አመራሮችን ያካተተ ልዑካን Familiarization Trip ሀገራችን ላይ በቅርቡ ለማድረግ መወሰናቸውን ገልፀውላቸዋል። በውጤቱም በጀርመን በሚገኙ 10 ሺህ የሚደርሱ የጉዞ ወኪሎች አማካኝነት የሀገራችንን የቱሪስት መዳረሻዎችና አማራጮች ለጀርመን ለማስተዋወቅ ዝግጁ መሆናቸዉን ሓላፊዉ ለክቡር አምባሳደር ፍቃዱ ገልጸዉላቸዋል።

 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook