ክቡር አምባሳደር ፈቃዱ በትውውቅ ውይይታቸው ወቅት አገራችን በትምህርቱ ዘርፍ እያስመዘገበች ያለውን ስኬቶች ያብራሩ ሲሆን ይህንን ስኬት ለማስቀጠል የሃገራችን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች ጋር እያደረጉት ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብርና ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉና እስካሁን ላደረጉትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በውይይቱ ወቅትም የዩኒቨርሲቲው ተወካዮች በበኩላቸው የሃገራቸውን የተለያዩ የከፍተኛ ተቋማት ልምድ ለሃገራችን ለማካፈልና በቅንጅት ለመስራት በተለይም በኢንዱስትሪው መስክ ያለውን ልምድ ለማካፈል በተለይም በጨርቃጨርቅና አልባሳት ላይ የተጀመረውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ጠቅሰው ኤምባሲው እያደረገ ያለውን ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም ከኤምባሲው ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook