የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በጀርመ አገር ከተካሄደው Berlin Energy Transition Dialogue.23 ተሣትፎ በተጨማሪም ከጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር /German-African Business Association Afrika-Verein/ CEO ከሆኑት Mr. Christoph Kannengiesser እና በኢነርጂ ዘርፍ ከተሰማሩ 14 የጀርመን ቢዝነስ ተቋማት ሓላፊዎችና ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ በትብብር በሚሰሩ ጉዳዮች ዙሪያ ክቡር ሚኒስትሩ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነም የጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር /German African Business Association Afrika-Verein/ ለአገራችን እያደረገ ላለው የተለያየ እገዛ በማመስገን ይኸው ድጋፍ በበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
የጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር /German-African Business Association Afrika-Verein/ CEO የሆኑት Mr. Christoph Kannengiesser በበኩላቸው ኢትዮጵያ በድርጅታቸው ትኩረት ከሚሰጣቸው አገራት ግንባር ቀደም አገር መሆኗን በመግለፅ በሁሉም መስክ ድጋፍና ትብብራቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
ጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር Africa-Verein ከሚያደርግው የተለያየ እገዛ በተጨማሪ በአገራችን በተለይም በኢነርጂ ዘርፍ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲሰሩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነም እ.አ.አ ኤፕሪል 26-28 2023 በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ “Invest and Grow in Ethiopia: The Land of Attractive Opportunities ” በሚል መርህ ቃል በሚዘጋጀው የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ እንዲሳተፉ በዉይይቱ ወቅት ጥሪ አቅርበዋል ።
 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook