በጀርመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ ከኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራ ሴቶች ማሕበር በጀርመን (EDWA) ጋር በመተባበር 129ኛውን የአድዋ ድል በዓል በጋራ በበይነ-መረብ አክብረዋል። በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ እንዲሁም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም የአሁኑ ትውልድ የዘመናችን አድዋ በሆነው የሕዳሴ ግድቡና ሌሎች ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በአንድነትና በሕብረት በመቆም ሀገርን ማሳደግ እንደሚገባ ጥሪ አስተላልፈዋል። ተሳታፊዎች የሕዳሴ ግድብ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመግለጽ፤ ለግድቡ ግንባታ የሚውል የ€4600 ቦንድ ለመግዛት ቃል ገብተዋል። በመድረኩ ወቅታዊ በሆኑ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ለማድረግ ተችሏል።

   

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook