(በርሊን ጀርመን ፣ ጥቅምት 4፣ 2017 ዓ.ም) 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን አምባሳደሮች ፣ ዲፕሎማቶች ሰራተኞች እንዲሁም ኢትዮጵያውያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በኤምባሲው ጽ/ቤት ቃለ መሓላ በመግባት እና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል ፡፡
ቀኑ “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ የተከበረ ሲሆን ክቡር አምባሳደር እስክንድር ይርጋ በጀርመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ኤምባሲ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልእክተኛ ባስተላለፉት መልእክት ሰንደቅ ዓላማ ኢትዮጵያውያን በደረሱበት የዓለም ክፍሎች ይዘውት የሚጓዙት ትልቁ ስንቅና ትጥቅ በልባቸው የተሳለው የሰንደቅ ዓላማ ክብርና ፍቅር ነው ብለዋል። የሰንደቅ ዓላማ ቀን ሲከበር አንድነትን እና ልማትን ይበልጥ በማጎልበት፤ ጠንክረን በመስራት ድህነትን ታሪክ በማድረግ ሰንደቅ አላማችን በአለም ደረጃ ከፍ ብሎ እንዲታይ ማድረግ ይገባል በማለት ገልጸዋል።
በበዓሉ የታደሙ አምባሳደሮች ፣ ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች የሀገራችን ሉዓላዊነትና ክብር ለማስጠበቅና በአንድነትና በጋራ ሰሜት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶች ለማሳካት በተሰማሩበት የስራ መስክ በትጋት እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል፡፡