በበርሊን 2024 ማራቶን አትሌት በወንዶች ማራቶን ሚልኬሳ መንገሻ ርቀቱን 2 ሠዓት ከ3 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ በማጠናቀቅ ውድድሩን ማሸነፍ ችሏል፡፡ እንዲሁም አትሌት ሐይማኖት አለው 2 ሠዓት ከ3 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል፡፡
የሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 4 በመውጣት አሸንፈዋል፡፡
በዚሁ መሠረት አትሌት ትዕግስት ከተማ ርቀቱን 2 ሠዓት ከ16 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ በመግባት አሸንፋለች፡፡ እንዲሁም አትሌት መስታወት ፍቅር 2 ሠዓት ከ18 ደቂቃ ከ48 ሠከንድ በመግባት 2ኛ፣ ቦስና ሙላቴ 2 ሠዓት ከ19 ደቂቃ ርቀቱን በማጠናቀቅ 3ኛ እና አበሩ አያና 2 ሠዓት ከ20 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ በመግባት 4ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡
የኤምባሲው ሰራተኞች እና ዲያስፖራዎችም በቦታው በመገኘት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook