የአዲስ አበባ አደበባይና የአዲስ አበባ አደባባይ ትምህርት ቤት በጀርመን ላይቭዚግ ከተማ ተመረቀ።
የአዲስ አበባ መጠሪያን የያዘ በጀርመን ሃገር በላይቭዚግ ከተማ ከተማ የሁለቱን ከተማ የእህትትማማችነት ደረጃ የሚያጠናክርና ወደ ከፍተኛ ደረጃ የሚያደርስ አደባባይና ትምህርት ቤት ተመረቀ።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ወቅት የላይቭዚግ ከተማ ከንቲባ የሆኑት Mr. Burkhard Jung (Burkhard Jung) በአዲስ አበባ ከተማ ስም የተሰየመው አደባበይና ትምህርት ቤት የሁለቱን ከተሞች የቆየ ትብብር እየተጠናከረ መሄዱን የሚያሳይ መሆኑንና ወደፊት በተለያዩ ዘርፎች ያሉ ትብብሮች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅሰዋል።በአደባባይና በትምህርት ቤት ስያሜ ምረቃ ወቅት የአዲሰ አበባ ከንቲባን ክብርት አዳነች አቤቤን (Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ ) ወክለው መልዕክት ያስተላለፉት የከተማው አስተዳደር ካቢኔ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ዶ/ር አሻግሬ ገብረ ወልድ በበኩላቸው የክብርት ከንቲባዋን መልዕልት ሲያስተላልፉ ታሪካዊ በሆነችው በላይቭዚግ ከተማ ላይ አዲስ አበባ የአደባባይና የትምህርት ቤት ስያሜ መሰጠቱ የሁለቱን ከተሞች ትብብር ያለበትን ደረጃ ያሳየ መሆኑንና አዲስ አበባም የአፍሪካ መዲና፣የተለያዪ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰቦች መቀመጫ እንደመሆኗ ከላይቭዚግ ከተማ ጋር በተለያዩ መስኮች እያደረጉት ያለውን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉና. የላይቭዚግ ከተማ (Stadtverwaltung Leipzig )ላደረገላቸው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።
አዲስ አበባ እና ላይቭዚግ ከተማ የእህትማማችነት ከተማ ወዳጅነት የመሰረቱበትን 20ኛ አመት በማክበር ላይ ናቸው።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook