በርሊን ፤ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም :- የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ በርሊን ዲፕሎማቶችና ሠራተኞች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ አሻራቸውን አኑረዋል።
የኤምባሲው ዲፕሎማቶችእና ሠራተኞች በጀርመን በርሊን በሚገኘው የኤምባሲው ቅጥር ግቢ ዉስጥ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን ያኖሩት።
በመርሀ ግብሩ ላይ የሚሲዮኑ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ሃይላይ ብርሃነ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም እንዳደረገችዉ ሁሉ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል የተያዘው እቅድ እንደሚሳካ እምነታቸውን ገልጸዋል ።
በተወከልንበት ሀገር ለአገራችን ገጽታ ግንባታ ትልቅ ፋይዳ ስላለዉ ኢትዮጵያ የክብረወሰን ባለቤት እንድትሆን መረባረብ አለብን ብለዋል አምባሳደር ሃይላይ በመልዕክታቸው፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook