የማህበሩ ምስረታ መርሃ ግብር በንግግር የከፈቱት የሚሲዮኑ ምክትል መሪ አምባሳደር ተፈሪ ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያዉያን ዳያስፖራ ሴቶች በተናጠል ወይም በግላቸዉ የሀገራቸዉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለማቃለል የተለያዩ ዓይነት ድጋፎችን ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ እና በእዉቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር በመሳተፍ አበረታች ስራዎችን ሲያከናወኑ ቆይተዋል፡፡

ነገር ግን ዳያስፖራ ሴቶች  በመሰረቱት ማህበር አማካይነት እዉቀታቸዉን፣ ልምዳቸዉን እና ሌሎች አቅሞቻቸዉን በማቀናጀት በተደራጀ መልክ ቢንቀሳቀሱ የሚያጋጥማቸዉን ችግሮችን በሕብረት በመፍታት እራሳቸዉን እና ሕዝባቸዉን የሚጠቅሙ ዉጤታማ ስራዎችን ለማከናወን እንደሚያግዛቸዉ በመግለጽ ሁሉም በጀርመን እና ሚሲዮኑ በተወከለባቸዉ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ሴቶች የማህበሩ አባል እንዲሆኑ እና ጠንካራ ማህበር ለመፍጠር በትጋት እንዲሰሩ በማሳሰብ በጀርመን የኢትዮጵያዉያ ኤምባሲ ማህበሩ በሚያደርገቸዉ በጎ ተግባራት ሁሉ  አስፈላጊዉን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ቃል በመግባት አረጋግጠዋል፡፡

በመቀጠል የማህበሩ ምስረታ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ለማህበሩ ምስረታ የተደረገዉን ዝግጅት በተለይም የማህበሩ ቻርተር፣ ዓላማና የትኩረት አቅጣጫዎችን  በማብራራት ካቀረቡ በኃላ ከተሳታፊዎች አስተያየትና ጥያቄዎች ቀርበዉ ዉይይት ከተደረገ በኃላ በማህበሩ አባልነት በመሳተፍ አስተዋጽኦ ለማድረግ ቃል በመግባት ስብሰባዉ ተጠናቋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook