ኤግዚቢሽኑ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ትስስር መፍጠር ላይ ትኩረት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ከመላዉ ዓለም ከዘርፉ 170 በላይ አገሮች እና 5ሺ 5መቶ የሚጠጉ ቱር ኦፕሬተሮች ፣ ሆቴሎች፣ አየር መንገዶች እና የዘርፉ አማካሪ ድርጅቶች ተሣትፎ አድርጓል። በኤግዚቢሽኑ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢምባሲ በርሊን አስተባባሪነት ከሀገራችን ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከክልል የቱሪዝም ቢሮዎች እና አስጎብኚዎች የተውጣጡ 20 የትርኢቱ ተሳፊዎች ስራዎቻቸውን አቀርበዋል። ኢትዮጵያ በክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር መሪነት በተመራ ቡድን ከፍተኛ ተሣትፎ ያደረገች ሲሆን ኢትዮጵያ በዘርፉ እያከናወነች ያለዉን ተግባራት እና ቱሪዝም የኢትዮጵያ መንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ለዓለማችን የቱሪዝም ዘርፍ የየሀገራት ተወካዮች እና ለታላላቅ የቱር ኦፕሬተሮች ገለጻ አድርገዋል። በቱሪዝም ኤግዚብሽን መድረኩ የቱሪዝም ትስስር መፍጠር የተቻለ፣ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ የቱሪዝም ፕሮሞሽን ከኢትዮጵያ የቡና ጠጡ ሴሪሞኒ ጋር በከፍተኛ ሁኔታ መስራት ተችሏል ።
   
 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook