128ኛው የአድዋ ድል በዓል በጀርመን የኢፌዲሪ ኤምባሲ በድምቀት ተከበሯል፡፡ “ዓድዋ: የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል የተከበረው የዘንድሮው በዓል በጀርመንና በፖላንድ በሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ዲፕሎማቶች ታድመዋል፡፡

በበዓሉ ላይ በጀርመን የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ባስተላለፉት መልዕክት የዓድዋ ድል ለኛ ለኢትዮጵያውያን የድላችን ዓርማና ምልክት፣ የአንድነታችን ካስማ የኩራታችን ምንጭ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሊኮራበት የሚገባ ነው ብለዋል::

ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ አያይዘው የአሁኑ ትወልድ በዓሉን ሲያከብር ከአድዋ ደወል ተምረን ለሃገራችን በተለያየ መስክ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ነው ብለዋል፡፡

በበዓሉ ላይ የታደሙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዓሉ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ መሆኑን አውስተው ዛሬም እንደ አያት ቅድመ አያቶቹ ለሃገሩ የበኩሉን መወጣት እንዲችልና በዘመናችንም አዲስ ታሪክ በመስራት ለመጪዉ ትዉልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ መልእክት
አስተላልፈዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook