ክቡር አምባሳደር ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ የገለፁ ሲሆን ዳይሬክተሯ በበኩላቸው በቆይታቸው መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
በተጨማሪ ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ ከቼክ ሪፐብሊክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰብ ሰሃራ አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ከሆኑት Mr. Vaclav Prasil ጋር ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን ሁለቱ ሃገሮች በሁለትዮሽ፣በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ በትብብር ለመስራት እና ግንኙነቱን ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በተመሳሳይ ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ የቼክ ውጭ ጉዳይ የልማት ትብብር እና ሰብአዊ እርዳታ ዳይሬክተር ከሆኑት Mr. Petr Gandalovic ጋርም የተወያዩ ሲሆን ቼክ ለሃገራችን የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥል የጠየቁ ሲሆን ዳይሬክተሩም ትብብሩ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook