(የካቲት 01 ቀን 2016ዓ.ም ) በጀርመን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ልዩ መልእክተኛ እና ባለሙሉሥልጣን ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ከ Dipl.-Ing. Knut Stegemann የEMT HANDELS-WAREN Company Manager እና Prof.Dr.Ing. Peter Hartwig የ Aaqua &Waste International GmbH Managing Director ጋር በኤምባሲው ተዋያይተዋል ።
በውይይቱም የሁለቱ ካምፖኒ ማኔጀሮች ስለካምፖኒያቸዉ ገለጻ ለክቡር አምባሳደሩ ያቀረቡ ሲሆን EMT HANDELS-WAREN በዘመኑ ቴክኖሎጂ በባትሪ የሚሰሩ የዲሊቨሪ ሞተር እና ተሽከርካሪ የሚያመርት ፤ Aaqua &Waste International GmbH ደግሞ በመኖሪያ ቤቶች ላይ የሚገጠሙ የንጹህ መጥቶ ዉሃ ቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶችን አስተዋዉቀዋል። በኢትዮጵያ በቅድመ ቢዝነስ ጉዞ እና ኢንቨስትመንት ጉብኝት ለማድረግ ፍላጐት እንዳላቸው ለአምባሳደሩ ገልጸዋል ።
ክቡር አምባሳደር በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ ስላለው የኢንቨስትመንት ዕድሎችና አማራጮች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ካምፖኒዎቹ ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ ፍላጎት ማሳየታቸዉን በማመስገን ኤምባሲው ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ገልጸውላቸዋል ::