FRUIT LOGISTICA አዉደ ርዕይ በየዓመቱ በበርሊን የሚካሄድ የፍራፍሬ ሎጂስቲክስ ምርት ኢንዱስትሪ እና ለአለም አቀፍ ገበያ የሚገናኙበት በፍራፍሬ Exhibition በአለም የመጀመሪያ የንግድ ትርኢት ነው።

ከሀገራችን Ethiopian Horticulture Producer
Exporters Association
(EHPEA) ተወካዮች እና የዘርፉ ካምፓኒዎች ስድስት ዋና ዋና አምራቾች የተሣተፉ ሲሆን በFRUIT LOGISTICA አዉደ ርዕዩ ላይ በኢትዮጵያ የተመረቱ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች በማስተዋወቅ የንግድ ትስስርም ተፈጥሯል ።

በጀርመን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በአዉደ ርእዩ ተገኝተው የኢትዮጵያ ኤግዚቢተሮች ያበረታቱ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ላይ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን በመጥቀስ ዓለም የገበያ ትስስር ለመፍጠር አዉደ ርዕዩ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook