(ታህሣስ 15 ቀን 2016ዓ.ም ) በጀርመን የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛ እና ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በጀርመን ከሚኖሩ Ethiopian Brothers and Sisters in German የዳያስፖራ አደረጃጀት አባላት ጋር በዌብነር ተወያዩ።
በመድረኩ በአገራችን የሚከሰቱ የውስጥ ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት መንግስት እያከናወናቸው ስላሉ ስራዎች፣ የቆዩ የአለመግባባት ምንጭ የሆኑ ገዳዮችን ለይቶ በዘላቂነት ሰላምን በአገራችን ለማስፈን በአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት እንዲሁም የአገራችን የባህር በርና ወደብ አጠቃቀም መብትን በተመለከተ፣ በኢትዮጵያ እና በጀርመን መካከል ስላለዉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት እና በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ከዳያስፖራ አባላቱ ጋር ስለሚሰሩ ስራዎች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎች በአምባሳደር ፍቃዱ በየነ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል::
የዳያስፖራ አባላቱም ወቅታዊ መረጃን ኮሚሲዮን መሪ በቀጥታ ለማግኘት የቻሉበት መድረክ በመመቻቸቱ መደሰታቸውን በመግለጽ ለዳያስፖራው ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ከተቻለ አገራቸውን በሚችሉት ሁሉ ለማገዝ ዛሬም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በጀርመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልእክተኛ እና ባለሙሉሥልጣን ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በመድረኩ ማጠቃለያ Ethiopian Brothers and Sisters in German የዳያስፖራ አደረጃጀት አባላት በውይይቱ ለነበራቸው የነቃ ተሳትፎ አመስግነው በቀጣይም ከሚሲዮኑ ጋር በመቀናጀት ሀገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ስራዎችን በጋራ ለመስራት እንደሚገባ በማስገንዘብ ኤምባሲው ለዳያስፖራው ማህበረሰብ አስፈላጊው ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል