(በርሊን፡ ታህሳስ30  ቀን 2016 ዓ.ም) በበርሊን የኢፌዴሪ ኤምባሲው ለሁለተኛ ትውልድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በጀርመን እና ሚሲዮኑ በሚሸፍናቸዉ ሀገራት ከሚገኙ የዳያስፖራ አደረጃጀት እና የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ጋር የዉይይት መድረክ አካሄደ።
በዉይይት መድረኩ ላይ በጀርመን የኢፌዴ.ሪ ምክትል ሚሲዮን አምባሳደር አምባሳደር ተፈሪ ታደሰ፣ የተለያዩ የዳያስፖራ ደረጃጀቶች ወላጆች ፣ የሁለተኛው ትወልድ ወጣት ዳያስፖራዎች፣ የጉዲፈቻ ማህበር ተወካዮች ፣ የሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም የሚሲዮኑ ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ተፈሪ ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት መላው ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው በመጓዝ ስለሀገራቸው ባህልና ታሪክ እንዲያውቁና እንዲተሳሰሩ፣ የሀገር ፍቅር ስሜታቸውን እንዲያጎለብቱና ሀገራቸውን ለተቀረዉ ዓለም እንዲያስተዋዉቁ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የቀረበው ሀገራዊ ጥሪ ታሪካዊ ዕድል የሚፈጥርላቸው መሆኑን ጠቁመዋል። በጀርመን እና ሚሲዮኑ በሚሸፍናቸዉ የሚገኙ የሁለተኛ ትውልድ ዳያስፖራ አባላት ጥሪውን በመቀበልና ወደ ሀገር ቤት በመጓዝ ተጨባጭ ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪውን በይፋ አቅርበዋል፡፡ ጥሪውን በመቀበል ወደ ሀገር ቤት የሚጓዙ የዳያስፖራ አባላት ስኬታማ ቆይታ እንዲኖራቸው በሀገር ቤትና በኤምባሲው አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁንም አክልው ገልጸዋል፡፡
የጥሪውን ዓላማና መርሃ ግብሮች አስመልክቶ ዝርዝር ገለጻ የቀረበ ሲሆን፣ በመድረኩ ላይ የተሳተፉ የዳያስፖራ የአደረጃጃት ተወካዮችና የሁለተኛ ትውልድ ወጣት የዳያስፖራ አባላት በበኩላቸው ጥሪው የሀገር ፍቅርን የሚቀሰቅስና የባለቤትነት ስሜትን የሚያጎለብት መሆኑን በመጠቆም በመጀመሪያ ዙር የሀገር ቤት ግቡ ጥሪ ወቅት የሰጡትን ተጨባጭ ምላሽ ለመድገምና ወደ ሀገር ቤት በመጓዝ በተዘጋጁት ኩነቶች ላይ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook