በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ በሆኑት ክቡር አቶ ሀሰን ሙሃመድ እንዲሁም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ በሆኑት ዶ/ር ባዪሳ በዳዳ የተመራ ልዑክ በኤምባሲው በመገኘት ከክበር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ጉብኝቱ GIZ እና KFW ከተባሉ የጀርመን አገር የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ዓላማውም የአገራችንን የግል ሴክተር ልማት ለማጎልበት በተለይም በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ዙሪያ ያሉ ተሞክሮዎችን ለመውሰድ ያለመ ነው።
የልዑካን ቡድኑ በአገራቸን በግሉ ዘርፍ ኢንቨስተመንት በኩል እየመጡ ያሉ የአሰራር፣ የፖሊሲ እና የህግ ማዕቀፍ መሻሻሎችን በማንሳት በኤምባሲው በኩል ድጋፍ እና ክትትል የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ከክቡር አምባሳደር ጋር ውይይት የደረጉ ሲሆን፤ ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በበኩላቸው GIZ እና KFW የተባሉ የጀርመን አለምአቀፍ የልማት ድርጅቶች በአገራችን የሚያደርጉት ድጋፍ ተጨባጭ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ክቡር አምባሳደር በኢትዮጵያ እና ጀርመን መካከል የሚገኘውን መልካም የሁለትዮሽ ግንኙነት በተመለከተ ለልዑካን ቡድኑ ገለጻ አድርገው፣ ለልምድ ልውውጡ ስኬታማነት የኤምባሲው ክትትልና ድጋፍ እንደማይለያቸው ገልጸዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook