ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በቅርቡ በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ ሆነው ከተመደቡት Dr. Ferdinand von Weyhe ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።
አምባሳደር ፍቃዱ Dr. Weyhe ለዚህ ኃላፊነት በመታጨታቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ ከዚህ ቀደም ያላቸው የረዥም አመታት የዲፕሎማሲ ልምድ ለቀጣዩ ተልዕኳቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
Dr. Weyhe በበኩላቸው የጥንታዊ ባህል እና ኃይማኖቶች ባለቤት ወደ ሆነችው አገር ለመሄድ በመዘጋጀታቸው ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለመሻሻል እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት፣ የሽግግር ፍትህ እና የብሔራዊ መግባባት ኮሚሽን እስካሁን ያሉበትን ሂደት እና አፈጻጸም በማጋራት በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ እየመጡ ያሉ መሻሻሎችን አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ለDr. Ferdinand von Weyhe በአዲስ አበባ ውጤታማ እና መልካም የስራ ዘመን እንዲኖራቸው ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል።

 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook