(ሐምሌ 10፣2015 ዓ.ም ) በበርሊን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉስልጣን ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ እና የሚስዮኑ ባልደረቦች በተገኙበት የአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በበርሊን የኢፌዲሪ ኤምባሲ ጽ/ቤት ተካሂዷል።
ክብር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በተዘጋጀዉ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር በመላዉ ሀገራችን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አነሳሽነት በየዓመቱ እየተካሄደ ያለው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ኢትዮጵያን አረንጓዴ በማልበስ በአየር ንብረት ለውጥ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቀነስ ትልቅ ፈይዳ እንዳለው ገልጸዋል ።