(ሰኔ 11 ቀን 2015 ዓ/ም በርሊን ): ይሄ የተገለጸዉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በጀርመን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ምሁራን ጋር የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ላይ በበየነ መረብ በተወያዩበት ወቅት ነው ።
በዉይይት መድረኩ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ የተገኙ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ተከላ ዝግጅት 500 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ቀን በሚተከልበት ዋዜማ ላይ የተደረገ በመሆኑ መድረኩን ልዩ እንደሚያደርገዉ በማዉሳት በአገራችን ባለፉት አራት አመታት 25 ቢሊዮን ችግኝ መተከሉንና በአረንጓዴ አሻራ እንደአገር እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ላይ ገለጻ በማቅረብ የተያዘዉን ፕሮግራም ይበልጥ ዉጤታማ ለማድረግ በጀርመን እና አከባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ምሁራን በሀሣብ ፣ በእዉቀት እና በገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
በመድረኩ የተሣተፉት በጀርመን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚያስተምሩ እና በተለያዩ የጀርመን ተቋማት ዉስጥ በሞያቸው በጤና ዘርፍ ፣ በትምህርት ፣ በሕግ ፣ በምርምር እና በማኔጅመንት የሚያገለግሉ ሲሆን ምሁራኑ በአረንጓዴ አሻራ ያላቸዉን ትምህርት ፣ ልምድና ተሞክሮአቸውን አቅርበዋል ።
ከምሁራኑ መካከል በሳይንቲስት ተስፋዬ ውበት በጀርመን ዩኒቨርሲቲ መምህራና ተመራማሪ በችግኝ ጥራትና ዉጤታማነት ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን የክቡር ሚኒስቴር ዴኤታዉንና የሳይቲስቱን ገለጻ ተከትሎ ከተሣታፊዎቹ ጥያቄ እና አስተያየትን በማንሳት በመድረኩ ዉይይት ተደርጎበታል ።
የኢትዮጵያ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ምሁራን በተማሩበት እና በሚሰሩበት ሞያቸዉ ሀገራቸዉ በአረንጓዴ አሻራ ለምታደርገው እንቅስቃሴ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል ።
በዉይይቱ የተሳተፉ ምሁራንም በዚህ መድረክ በመገናኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ በቀጣይ በተማሩበት እና በተሰማሩበት የሞያ ዘርፍ ኢትዮጵያ የጀመረችዉን የአረንጓዴ አሻራ እንደየሞያቸዉ ተደራጅተው ለማገዝ ፍላጎታቸው መሆኑን በመግለጽ በተጠየቀው መሠረትም ፕሮግራሙን በሀሳብ፣ እውቀት እና በገንዘብ እንደሚደግፋ ቃል ገብተዋል ።
   

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook