(ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ) በጀርመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በጀርመን ሀምቡርግ ከተማ መቀመጫውን ካደረገ የConjuncta GmbH CEO ከሆኑት Professor Dr. Stefan Liebing በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አድርገዋል።

ክቡር አምባሳደሩ Professor Dr. Stefan Liebing የጀርመን  አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር የቦርድ ስብሳቢ ሆነው በሰሩባቸው  የአመራር ጊዜያት የጀርመንና የአገራችንን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማሳደግ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነው፤ የአገራችንን  የኢንቨስትመንት አማራጮች እና እድሎች እንዲሁም በተመረጡ አገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ  ገለጻ አድርገውላቸዋል። 

Professor Dr. Stefan Liebing  በበኩላቸው ድርጅታቸው በኢንቨስትመንትና በፕሮጀክት አስተዳደር የሚሰራ ሰፊ ተደራሽነትና አቅም ያለው የኢንቨስትመንት ድርጅት መሆኑን በመግለጽ  በጋራ አብሮ ለመስራት የሚቻልባቸው የትኩረት መስኮች በመሆናቸው በተለይ በፋርማሲዪቲካል፣በአይሲቲ  እንዲሁም በኢነርጂ ዘርፍ በተመረጡ ፕሮጀክቶች ላይ በጋራ በትብብር ኢንቨስት ማድረግ እንደሚቻልም ለክቡር አምባሳደሩ ገልጸውላቸዋል።

በዉይይቱ ማጠቃለያ ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ  ፕርፌሰሩ በConjuncta GmbH የኢንቨስትመንትና የፕሮጀክት ማኔጅመንት ድርጅት ሓላፊነትነታዉ በተመረጡ አገራዊ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ተግባራዊነት ትብብርና ድጋፍ ጠይቀዋል ።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook