(ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም )በጀርመን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክሪሲያዊ ሪፐብሊክ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክብር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ከብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ወቅትም ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ኤምባሲያችን ከቤተክርስቲያኒቷ ጋር በሀገራዊ ጉዳይ ላይ በመተባበር አብሮ ሕዝባቸዉን ሲያገለግሉ መቆየታቸዉን በማስታወስ ምዕመናኑን በማስተባበር አስተባብረው ሲያደርጉ ለነበረውና አሁንም ብፁዕነታቸው በኤምባሲዉ ስለተገኙ ምስጋና አቅርበዋል።
በውይይቱም ክብር አምባሳደሩ ኤምባሲው የሚያከናዉናቸዉን ተግባራት ለብፁነታቸዉ ያብራሩ ሲሆን፣ ከቤተክርስቲያኗ ጋርም አብረው እንደሚሰሩ ገልጸዉላቸዋል ።
ክብር አምባሳደር በማያያዝም ከፈጣሪ የተሰጠችን ለሁላችንም አንድ የሆነችውን ሀገራችንን ለመደገፍ ተባብረን በጋራ በመቆም ቤተክርስቲያኗ እንደከዚህ ቀደሙ አርአያነቷን እንድትቀጥል አምባሳደር ፍቃዱ ጠይቀዋል።
በዉይይቱ ወቅትም ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ጠብቃ ከመንግሥት ጋር ሕዝቧን የማገልገል የቀደመ ታሪክ እና ልምድ ያላት ቤተክርስቲያን መሆኗን በማስታወስ አሁንም ችግሮችን ተቀራርቦ በዉይይት በመፍታት ተቀራርቦ በመስራት የጋራችን የሆነችውን ሀገራችንንና ሕዝባችንን ማገልገል አለብን ብሏል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook