በጀርመን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ክቡር አምሳሳደር ፍቃዱ በየነ ሚሲዮኑ በሚሸፍናቸዉ ሀገራት ከሚገኙ የዳያስፖራ አደረጃጀት ኃላፊዎችና ተወካዮች እንዲሁም ከቢዝነስ ባለቤቶች ጋር ውይይት አደረጉ።
================================
(ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በጀርመን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አምሳሳደር ፍቃዱ በየነ በሀገሪቱ ከሚገኙ ከ48 በላይ የዳያስፖራ አደረጃጀት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ውይይት አደረጉ።
ውይይቱም ኤምባሲው በሚያከናውናቸዉ ተግባራት ፣ ስለአገልግሎት አሰጣጥ፣ ወቅታዊ ሁኔታ ጉዳዮች ፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፣ የገበታ ለትውልድ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች እና የዳያስፖራው ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ነበር።
ክቡር አምባሳደሩ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ኤምባሲው የሚያከናዉናቸዉን ተግባራት ዳያስፖራዉ እንዲያዉቀዉ ግንዛቤ ያስጨበጡ ሲሆን በሀገራችን መንግስት ትኩረት በመስጠት እያከናወናቸዉ ሁሉን አቀፍ የልማት ስራዎች አብራርተው የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ባሉ መላው ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ እና ርብርብ የግድቡ ስራ 91% መድረሱን እና በገበታ ለትዉልድ ፕሮጄክት ለመጪው ትዉልድ የምትመጥን ኢትዮጵያን ለመገንባት ታላላቅ የቱሪስት መዳረሻዎች እየተሰሩ መሆኑን ለአብነት አንስተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም የኤምባሲው የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል ፣ በሀገር ቤት አልፎ አልፎ የሚታዩ ችግሮችን ለውይይት ቅድሚያ እንዲሰጥ፣ ለዜጎች የኑሮ ውድነት ሁኔታ ትኩረት እንዲሰጥ እንዲሁም የመረጃ ፍሰት እንዲጎለብትና ሌሎች ተያያዥ ሃሳቦችን ያነሱ ሲሆን፣ ክቡር አምባሳደሩም ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራሪያ በመስጠት ዳያስፖራው ለሚያበረክተው ሁሉን አቀፍ ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ገልጸዋል ። እንዲሁም ሁሉም የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን የዜጋ ዲፕሎማሲን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መልእክት አስተላልፈዋል ።
ተሳታፊዎቹም ሀገራቸውን ለመደገፍ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንድሚቀጥሉም አስታውቀዋል።
 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook