(ሰኔ 05 ቀን 2015 ዓ/ም በርሊን ): የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በጀርመን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ምሁራን ጋር በበየነ መረብ ተወያይተዋል ።
በዉይይት መድረኩ የተሣተፉት በጀርመን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚያስተምሩ እና በተለያዩ የጀርመን ተቋማት ዉስጥ በሞያቸው በጤና ዘርፍ ፣ በትምህርት ፣ በሕግ ፣ በምርምር እና በማኔጅመንት የሚያገለግሉ ከ40 በላይ ፕሮፌሰሮችና ዶክተሮች ሲሆኑ በምዕራፍ አንድ መድረክ አምስት ምሁራን በክቡር አምባሳደሩ ጋባዥነት ተሞክሮአቸውን አቅርበዋል ።
በምሁራኑ የቀረበዉ ተሞክሮ በተማሩበት እና እየሰሩበት ባለዉ ሞያ በግልም በህብረትም በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች እያከናወኑ ያለዉን ተግባራት ላይ ሲሆን ገለጻውን ተከትሎ በመድረኩ ዉይይት ተደርጎበታል ።
የኢትዮጵያ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክብርት አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ምሁራን በተማሩበት እና በሚሰሩበት ሞያቸዉ ለሀገራቸዉ ለሚያደርጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ወደ ፊት ለሚያከናዉኗቸዉ ተግባራትም የኤምባሲው ድጋፍ እንደማይለያቸው ገልጸዉላቸዋል ።
በዉይይቱ የተሳተፉ ምሁራንም በዚህ መድረክ በመገናኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ በቀጣይ በተማረበት እና በተሰማሩበት የሞያ ዘርፍ አገራቸውን ለመገልገል ፍላጎታቸው መሆኑን ለክቡር አምባሳደሩ ገልጸውላቸዋል ።
ክቡር አምባሳደሩ አያይዘውም ሀገራችን በራሷ አቅም በማጠናቀቅ ላይ የሚገኘዉን የሕዳሴ ግድብ ስላለበት ደረጃ እና በገበታ ለትዉልድ ፕሮጄክት ለመጪው ትዉልድ የምትመጥን ኢትዮጵያን ለመገንባት ታላላቅ የቱሪስት መዳረሻዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን ገለጻ በማድረግ ምሁራኑ በእውቀት ፣ በሀሳብ ፣ በሞያ እና በገንዘብ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል ።
 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook