በጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም በፌዴራል ፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት በተከናወነ ደማቅ ስነ-ስርዓት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት H.E. Frank-Walter Steinmeier አቀረቡ።

ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ ከፕሬዝዳንቱ ጋር በነበራቸው ውይይት በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ እንደሚሰሩ የገለጹ ሲሆን ክቡር ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከርና ያላቸውን ፍላጎት በመግለፅ አምባሳደሩ በጀርመን አገር በሚኖራቸው ቆይታ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉላቸው ቃል ገብተዋል።

 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook