(ሚያዝያ 10 ቀን 2015 ዓ/ም በርሊን ): የኢትዮጵያ.ፌዴራላዊ .ዲሞክራሲያዊ .ሪፐብሊክ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በጀርመን፣ በፖላንድ ሪፐብሊክ እና በቼክ ሪፐብሊክ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን ጋር የመጀመሪያ የዌብነር ትዉዉቅ በማደረግ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል ።
በውይይታቸው ወቅትም ሀገራችን በለዉጡ ሂደቶች ላይ ያሳካቻቸዉ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ስኬቶች እንዲሁም የነበሩ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ገለጻ ተሰጥተዋል ።
ክቡር አምባሳደሩ በማስከተልም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች በጸጥታ አደረጃጀት ፣ የሽግግር ፍትህ ሂደት እና በታላቁ ህዳሴ ግድብ እንዲሁም በገበታ ለትዉልድ ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን አራተኛዉ የዉሃ ሙሌት በቅርብ ቀን የሚከናወን በመሆኑ እንደከዚህ ቀደሙ ዳያስፖራዉ በቦንድ ግዢና ስጦታ እንዲሣተፉ ጠይቀዋል።
ገበታ ለትዉልድ እጅግ ኢትዮጵያን የሚያኮራ ኢኮኖሚውን የሚያነቃቃ ሀገራዊ ፕሮጄክት በመሆኑ ዳያስፖራዉ እንዲሣተፍ ጠይቀዋል።በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችም ዳያስፖራዉ እዉነታዉን ብቻ በመረዳት ከሀገሩ ጎን መቆሙን እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በመጨረሻም አምባሳደሩ ከዳያስፖራው ምን ይጠበቃል የሚለውን በማንሳት ለተነሱት ጥያቄዎች በኤምባሲው አገልግሎት አሰጣጥ እና ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከቱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook