የካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በጀርመን የስቱትጋርት Max Planck Institute for Solid State Research ቤተመጽሐፍት በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ም/ሚሲዮን መሪ  አምባሳደር ተፈሪ ታደሰን  ጨምሮ ሌሎች የኤ  ምባሲው ተወካዮች በተገኙበት የምርምር ጆርናሎችና ሜጋዚኖች ለአብርሆት ቤተ መፃሕፍት እንዲደርስ ተበርክተዋል።

የተበረከቱት ጆርናሎችና ሜጋዚኖች ለከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች በተለይ ለፊዚክስና ኬሚስትሪ ዘርፍ እጅግ ተፈላጊ  መሆናቸው ተገልጿል።

በእለቱ አምባሳደር ተፈሪ የቤተመጻሕፍቱ የሥራ ሓላፊዎችን  ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነው መጽሐፍቶቹ ለአብርሆት እንዲደርስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook