ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በጀርመን ካሉት 16 የፌደራል ክልሎች አንዱ በሆነው ብሬመን ከተማ መንግስት (Bremen City State) በመገኘት ከUniversity of Bremen እና Constructor University አመራሮች ጋር በኢትዮጵያ ከሚገኙ የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት ለመተባበርና እና ለመስራት ስለሚቻልበት ሁኔታ ውይይት አድርገዋል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮቹ ከአገራችን አቻዎቻቸው ጋር ለመስራት ዝግጁነታቸውን የገለፁ ሲሆን ክቡር አምባሳደሩም ዩኒቨርሲቲዎቹ ለሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ኤምባሲው አስፈላጊውን የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጠዉላቸዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook