በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ “invest in women accelerate progress” በሚል መሪ ቃል እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ “ሴቶችን እናብቃ፤ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል የሚከበረዉ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ-በርሊን በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡
የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት አምባሳደር ተፈሪ ታደሰ የኢፌዴሪ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶችን ማብቃት የሴቶች የተሳታፊነትና የተጠቃሚነት መብት ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን የሀገርን ልማት እና ሰላም ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና እንደሚጨወት ከገለጹ በኃላ የሀገራችንን ሴቶች በማብቃት እንዲሁም በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የበኩላቸዉን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመቀጠል ወ/ሮ ሉላ ኑር በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አክቲንግ ጄኔራል ዳይሬክተር “ሴቶችን በማብቃት ልማትና ሰላምን ለማረጋገጥ የዳያስፖራ ሴቶች ሚና “ በሚል ርዕስ የዉይይት መነሻ ጽሑፍ አቅርበዉ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡
በፓናል ዉይይቱ ላይ የተሳተፉት ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ሴቶች በሀገራችን በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የበኩላቸዉን ለመወጣት እና ከሚሲዮኑ ጋር በቅንጅት ለመስራት ቃል በመግባት ይህንን እዉን ለማድረግ የሴቶችን አደረጃጀት ለመመስረት የሚያስተባብር ኮሚቴ በመሰየም ዉይይቱ አብቅተዋል፡፡