በኢትዮጵያና ጀርመን መካከል የሁለትዮሽ የፖለቲካ ምክክር ዛሬ የተደረገ ሲሆን፣ ምክክሩም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚረዱ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር።
ውይይቱን በኢትዮጵያ ወገን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓና አሜሪካ ጉዳዮች ተ/ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል የሆኑት አቶ እስክንድር ይርጋ የመሩት ሲሆን በጀርመን ወገን በጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የሰብሳህራን እና ሳህል ቀጠና ዳይሬክተር የሆኑት አምባሳደር ክሪስቶፍ ሬትስላፍ የፖለቲካ ምክክሩን መርተዋል።
በውይይቱም በዋናነት የሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የተሻለ መግባባት የተደረሰ ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በርሊን በነበራቸው ቆይታ ከቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ጋር በጋራ መግባባት ላይ የደረሱባቸውን ጉዳዮች ለመተግበር መሰረት የጣለ ነበር።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook