በበርሊን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማሕበር (EDWA) አባላት ጋር ባደረገው የበይነ መረብ ውይይት ከማህበሩ አባላት ጋር አብሮ ለመስራት የሚቻልባቸው የትብብር መስኮች ለይቷል፡፡ የአደረጃጀቱ መመስረት አባላት እርስ በእርስ ለመደጋገፍ፣ ከሀገራቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር እና ለአገር ግንባታ ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ ትልቅ መሰረት እንደሚጥል ግንዛቤ ተወስዷል፡፡ ሚሲዮኑ ሴቶች በጋራ ጉዳዮቻቸው በመደራጀታቸው ያለውን አድናቆት ገልጾ፤ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁነቱን አረጋግጧል። በማሕበሩ አመሰራረት እና የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሊቀመንበሯ ወ/ሮ ራኒያ ክንፈ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፣ በጀርመን ነዋሪ ሴት ኢትዮጵያዊያን በአባልነት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በኤምባሲው የአገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። በበበይነ መረብ ውይይቱ ከ66 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡