የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በጀርመን በርሊን እ.ኤ.አ ማርች 6,2023 በተካሄደዉ Twin Cities World Tourim Forum ላይ ተሳትፈዋል ።
ፎረሙ በየዓመቱ ከITB Berlin 2023 ኤግዚብሺን አንድ ቀን በፊት የሚዘጋጅ ሲሆን የቱሪዝም ከተማ መዳረሻዎች ትስስር በመፍጠር የተረጋጋ ቱሪዝም እንዲኖር ዘርፉን ለማሳደግ ያለመ ነው ።
የቱሪዝም ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ እጅግ ድንቅ የቱሪዝም መዳረሻዎች ያሏት ሀገር መሆኗንና በዘርፋ እያከናወነች ያለውን ተግባራት በመድረኩ አጋርተዋል ።

በተጨማሪም የቱሪዝም ሚንስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከተለያዩ አገራት አምባሳደሮች እና የቱሪዝም ሀላፊዎች ጋር የከተሞች ትስስር በመፍጠር ቱሪዝም ላይ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል ።

   

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook